የተፈጥሮ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተፈጥሮ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ጀምሯል፡፡
ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በወረቀት እና በበይ መረብ ሲሆን÷ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡
የማኅበራዊ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂ ብሔራዊ ፈተና ባለፈው ሣምንት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡