Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ250 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ250 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱንም የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ካሮልይን ቱርክ ፈርመውታል።

የገንዘብ ድጋፍና የብድር ስምምነቱ በመተግበር ላይ ያለው የኢትዮጵያ እድገትና የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት መርሃ ግብር ፖሊሲ ማስፈፀሚያ የሚውል መሆኑም ተገልጿል።

የድጋፍና የብድር ስምምነቱ በአጠቃላይ 250 የአሜሪካ ዶላር ወይም 8 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር ሲሆን፥ ከዚህም 125 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በብድር መልክ፤ 125 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በድጋፍ የሚለቀቅ ነው።

እንደዚህ አይነቱ የድጋፍና የብድር ስምምነቱ በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ሚና በማስፋፋት ኢኮኖሚዋ እንዲያንሰራራ እና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚረዳ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ እና መልካም አስተዳደር ተግባራትን በማስፈን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያፋጥን መሆኑም ተመልክቷል።

በአጠቃላይ የገንዘብ ድጋፍና ብድር ስምምነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሪፎርም ተግባራት እንዲሁም የሀገር በቀል ኢኮኖሚውን ተግባራዊነት ለማፋጠን የሚረዳ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም መንግስት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚፈጠሩ የፋይናንስ እጥረቶችን እንዲሸፍን እና በወረርሽኙ ምክንያት በኢትዮጵያ የሪፎርም አጀንዳ ላይ የሚፈጠር ጫናን ለማቅለል የሚረዳ መሆኑም ታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.