Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የሥራ እድል ፈጣራን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡

የከተማ አስተዳደርሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር በዚህ ወቅት እንዳሉት÷መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ እቃዎች ዋጋ ከቀን ወደ እየናረ እንደሚገኝ አንስተዋል ።

ችግሩን ለመቀነስም የዘርፉ ተዋናዮች በትብብር እና በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት፡፡

በአስተዳደሩ ላይ የሕግ የበላይነት ከማስከበር አንፃር በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ መናገራቸውንም የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፅዳት እና ውበት ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ያሉ ጠንካራ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመው÷ በቀጣይ ሌሎች መሰራት ያለባቸውን ስራዎች በትኩረት ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል።

በስራ እድል ፈጠራ ረገድ በከተማም ሆነ በገጠር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም አሁንም የሥራ አጥ ችግሮች እንደሚስተዋሉ አንስተዋል።

በተለይም በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ በሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ለዜጎች የሥራ እድልን ከመፍጠር አንፃር ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር በመፈተሽ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

ከግብርና ጋር ተያይዞ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸው÷ በቀጣይም የመስኖ ውሃዎችን በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን ከማጎልበት አንፃር በይበልጥ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር ከቤቲንግ የቁማር ቤቶች ጋር ተያይዞ በቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.