አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአፍሪካ ህብረት አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጋና አክራ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
45ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።
ስብሰባው የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የአፍሪካ ሕብረት የኮሚሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የቀጣናዊ ማህበረሰብ ተወካዮች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ዛሬ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
ስብሰባው የሕብረቱን በፈረንጆቹ የ2025 በጀትን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡