Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በ2016 የበጀት ዓመት ከ2 ቢሊየን 253 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር እንደገለጹት÷በክልሉ በ2016 የበጀት ከ2 ቢሊየን 243 ሚሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ 2 ቢሊየን 253 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል።

ገቢው የተሰበሰበው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ የታክስ እና ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከግብር አሰባሰብ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥራዎችን ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም የክልሉ ገቢን ለማጎልበት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.