የኢትዮጵያ ግሪን ኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳካት የአረንጓዴ ዐሻራ ወሳኝ ነው- በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግሪን ኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳካት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሚና ከፍተኛ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በአይሲቲ ፓርክ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር እንደ ሀገር የተያዘውን የአረንጓዴ ዐሻራ ራዕይ ለማሳካት የችግኝ ተከላ አስፈላጊ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የተተከሉት ችግኞች ውበት ከመሆን ባለፈ ኢትዮጵያ በግሪን ኢኮኖሚ የበለፀገች እንድትሆን እንደሚያስችሉ ገልጸው÷ ለእንክብካቤውም ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡