996 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 996 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ከእነዚህ መካከል 20 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ በተደረገው ጥረት እስካሁን ከ66 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡