የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት የኦክሲጅን እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ

By Feven Bishaw

June 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም መወሰኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡