Fana: At a Speed of Life!

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በጎፋ ዞን ከተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተረፉና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ ኮሚቴ በማቋቋም ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ጉዳት የደረሰባቸውና በሕይወት የተገኙ 10 ሰዎች በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ማርቆስ መለሰ አስታውቀዋል፡፡

ከአደጋው የተረፉና የተፈናቀሉ ወገኖችን በአካባቢው በተለያዩ ሥፍራዎች በጊዜያዊነት የማስጠለልና የዕለት ደራሽ ምግብ የማቅረብ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የአስቸኳይ አደጋ ጊዜ መልሶ ማቋቋሚያ ኮሚቴ ተቋቁሞ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩንም ገልጸዋል፡፡

አሁንም የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው÷ በዞኑ ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 157 መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.