የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ መመዝገቢያ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ መመዝገቢያ ይፋ መሆኑን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚሁ መሠረት በዚህ ማስፈንጠሪያ https://www.ethiocoders.et/ መመዝገብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡