Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክሩ ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ በመሆኑ የነቃ ተሳትፎ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ለኢትዮጵያ መጻኢ ዕድል ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን በመገንዘብ ሕብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጥሪ አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከወከሉ ከ1 ሺህ 200 በላይ ተመራጮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሥድስት ቀናት የሚቆይ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደሚኖርም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘገዬ አስፋው መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኮሚሽኑ እያከናወነ ያለው የምክክር ሂደት ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ለኢትዮጵያ መጻኢ ዕድል ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ እየተሳተፉ ያሉ አካላትም ከውይይት በኋላ ለአጀንዳነት የሚቀርቡ ጉዳዮችን አዘጋጅተው እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.