Fana: At a Speed of Life!

በመሬት መንሸራተት አደጋው ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ መገሆኑ ተገለጸ፡፡

ከመንግሥት በተጨማሪ የሕብረተሰቡ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህል ተጠናክሮ መቀጠሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ሰለሞን ገልጸዋል፡፡

ሕብረተሰቡ እንዲሁም አጎራባች ዞኖች እና አጋር የልማት ድርጅቶች እያደረጉት ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

እስከ አሁንም ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን የመደገፍ፣ በሕይወት የተረፉትን ሕክምና እንዲያኙ የማድረግ፣ ለጉዳት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያሉት ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር፣ ሰብዓዊ ድጋፎችን ማቅረብን ጨምሮ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.