አምባሳደር ታዬ ከስፔን የውጭና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጸሃፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከስፔን የውጭ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጸሃፊ ዲዬጎ ማርቲኔዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ረጅም ዓመታት የቆየውን የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡