በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ክልል አቀፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
የዘንድሮው የ2017 በጀት ዓመት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ“በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በግብርና፣ በከተማ ልማት፣ በማህበራዊ እና በሠላምና የሀገር ግንባታ መስኮች የተለያዩ በጎ ተግባራት እንደሚከናወኑም ተመላክቷል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ሁሉንም መዋቅሮች፣ የወጣቶችንና ሴቶች አደረጃጀቶችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል አደረጃጀቶችን በማቀናጀት ውጤታማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን ከማከናወን ባለፈ አብሮነትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡