Fana: At a Speed of Life!

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩት የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ 80 ወጣቶች ለ20 ቀናት በ11 ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በመዘዋወር የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ሲሰጡ መቆየታቸው  በመድረኩ ተመላክቷል።

በምስጋና መርሃ ግብሩ  የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር  ኤርጎጌ ተስፋዬ( ዶ/ር)÷ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው  የጎላ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሀገር ፍቅር በተግባር የሚገለፅበት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ በበኩላቸው÷ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተጀመረበት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የበጎ ፈቃደኞች ቁጥር እያደገ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ መርሀ ግብሩ የአካባቢን ባህል እና ወግ ከመለዋወጥ ባለፈ የህይወት ስንቅ የሚገኝበት ነው ብለዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ እና ፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.