Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል በገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ክልሉ በመጀመሪያ ዙር ድጋፉ የሰብአዊ ድጋፍ ቁሳቁስ፣ መድኃኒት እና የድንገተኛ ህክምና ያካተተ የድጋፍ ቡድን ወደ ስፍራው ማቅናቱን ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ እና በሲዳማ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር በአቶ አበራ ዊላ የሚመራ ቡድን በዛሬው ዕለት ወደ ስፍራው አቅንቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.