Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በሐረር የሚገኘውን የፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ፣ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የአመራር አባላት ተሳትፈዋል።

የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታው በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየተከናወነ ሲሆን÷ ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን በኢንተርፕራይዙ የቢሮ ምህንድስና ቡድን መሪ ሄኖክ መላኩ (ኢ/ር) ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ባለ 8 ወለል ህንጻን ጨምሮ የጤና ባለሙያዎች መኖሪያ ቤትና ሌሎችንም መገልገያዎች የሚያካትት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ አፈፃፀም 65 በመቶ መድረሱን ጠቁመው፤ በአንድ ዓመት ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በትኩረትና በጥራት እየተሰራ መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የተመራው ቡድን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ በማስገንባት ላይ የሚገኘውን የቢሮ እና የመኖሪያ ካምፕም ጎብኝቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.