የብሄራዊ ስፖርት ም/ቤትን በአዲስ መልኩ ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል አቅጣጫ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት አደረጃጀትን በመፈተሸ መልሶ ለማደራጀትና ወደ ስራ ማስገባት በሚቻልበ ሁኔታ ላይ አቅጣጫ መቀመጡን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀዛቅዞ የቆየውን የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ወደ ስራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በውይይቱም ለኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት የሚጠቅሙ በርካታ ሃሳቦች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷ችግር ፈቺ መንገዶች መለየታቸውን አመልክተዋል፡፡
ስፖርት እንደ ሀገር አንዱ የልማት ዘርፍ ከመሆኑም በላይ መንፈሰ ጠንካራ፣ ንቁና ጤነኛ ዜጋ ለመፍጠር ሁነኛው መሳሪያ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
በቀጣይ የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት አደረጃጀትን በመፈተሽ መልሶ ለማደራጀትና ተቀዛቅዞ የነበረውን ብሄራዊ ስፖርት ም/ቤት ወደ ስራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቅሰዋል፡፡