የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኮቪድ-19 በአፍሪካ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመከላከል ሃብቶችን ለማሰባሰብ በተሰየመው ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

By Tibebu Kebede

June 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኮቪድ-19 በአፍሪካ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመከላከል ሃብቶችን ለማሰባሰብ በተሰየመው ስብሰባ ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተሳተፉ፡፡

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኞች ሪፖርታቸውን ለመሪዎች አቅርበዋል፡፡

በወቅቱም ውጤታማ የሀብት አሰባሰብንና አጠቃቀምን ለማረጋገጥ አፍሪካ እንደ አህጉር በአንድ ድምጽ ተቀናጅቶ መስራት እንዳለባት ተገልጿል፡፡

በትናንቱ ስብሰባ ላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎችን ጨምሮ የዓለም አቀፍ ተቋማት የቀድሞ መሪዎች መሳተፋቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡