የኢትዮጵያንና የሩሲያን ግንኙነት የሚመጥን የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር ፍላጎት መኖሩ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን እና የሩሲያን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚመጥን የሩሲያ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር እንፈልጋለን ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ከሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር የተወያዩት ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷ በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ስለሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች ገለጻ አድርገዋል።
በገለጻቸውም የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለኢንቨስተሮች ዝግጁ የተደረጉ መሰረተ ልማቶችን በተመለከተም ማብራራታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ከኤምባሲዎች፣ ከዓለም አቀፍ ማህበራትና ልማት ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑም ተነግሯል።