አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) በጅግጅጋ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) በጅግጅጋ ከተማ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ችግኝ ተከላው የተከናወነው በጅግጅጋ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሥራ አመራር ኮሌጅ መሆኑን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢብራሂም ዑስማንን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም በችግኝ ተከላው መሳተፋቸው ተመላክቷል፡፡