የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።
“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አሻራቸውን እያኖሩ ነው።
በዛሬው ዕለትም ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ ያስተባበረው እና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የህብረተሰብ ክፍል የተሳተፈበት የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ ገፈርሳ አካባቢ ተከናውኗል።
በመርሀ ግብሩ ከተለያዩ ድርጅቶች የተውጣጡ ሰራተኞችና ታዋቂ ሰዎችም ተሳትፈዋል።
በቅድስት አባተ