Fana: At a Speed of Life!

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከህብረተሰቡ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህብረተሰቡ ለግድቡ ግንባታ ያደረገውን ድጋፍ፣ ትብብርና እገዛ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም÷ ከቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ ከ8100 ኤ አጭር የፅሁፍ መልእክት፣ ከፒን ሽያጭና ሌሎችም መንገዶች ገቢ ማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

በዚህም ለግድቡ ግንባታ 1 ቢሊየን 712 ሚሊየን ብር ድጋፍ መሰብሰቡን ገልጸዋል።

የግድቡን ግንባታ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ጥረትና ርብርብ የዜጎች ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.