ስፓርት

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም አቻ ተለያይተዋል

By Tibebu Kebede

June 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ከኖርዊች ሲቲ የተጫወተው ሳውዝሃምፕተን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

ዳኒ ኢንግስ፣ አርምስትሮንግ እና ሬድሞንድ የድል ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ምሽት 4 ሰአት ከ15 በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከማንቼስተር ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ባለሜዳዎቹ ቶተንሃሞች በመጀመሪያው አጋማሽ ጥር ወር ላይ ባስፈረሙት በርግዊን ጎል መሪ መሆን ችለው ነበር።

ከእረፍት መልስ የተጫዋች ቅያሪ ያደረጉት ማንቼስተር ዩናይትዶች ፖል ፖግባ ተጠልፎ ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ምት ብሩኖ ፈርናንዴዝ አስቆጥሮ አቻ መሆን ችለዋል።

በጨዋታው በተለይም ከእረፍት መልስ ማንቼስተር ዩናይትዶች የተሻለ የግብ እድል ቢያገኙም አጋጣሚዎቹን መጠቀም አልቻሉም።

ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬም ሲቀጥል ዋትፎርድ ከሌሲስተር ሲቲ፣ ብራይተን ከአርሰናል፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከወልቭስ እንዲሁም በርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ ይጫወታሉ።