87 በመቶ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አላላፉም ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 87 በመቶ የሚሆኑት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዘንድሮውን የመውጫ ፈተና ማለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡
እንዲሁም 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ነው የገለጹት፡፡
የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ማሳለፍ የቻሉት 13 በመቶ ብቻ ነው ማለታቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መረጃ አመላክቷል፡፡
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡