“እኛ ከሰራን እና ከተጋን ለውጡን በየጊዜው የምናየው እና የምንጠቀመው መሆኑን በደበል ተራራ ያለው ውጤት አሳይቶናል። ” ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ”እኛ ከሰራን እና ከተጋን ለውጡን በየጊዜው የምናየው እና የምንጠቀመው መሆኑን በደበል ተራራ ያለው ውጤት አሳይቶናል።” ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዳነች አቤቤ ይህንን የተናገሩት ÷ከተቋማቸውና ከተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ጋር በመሆን ችግኝ ተከላ ባካሄዱበት ወቅት ነው።
ችግኝ ተከላው የተካሄደው በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከሰበታ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ደበል ተራራ ነው።
ተቋሙ በ2012 ዓ.ም 60 ሺህ ችግኞችን ለመትከል የያዘውንየአረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ እቅድ በተግባር ለማረጋገጥ ችግኝ ተከላው ዛሬ መጀመሩ ተገልጿል።
ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎንም ከዚህ በፊት የተተከሉ ችግኞች የተጎበኙ ሲሆን 90 በመቶ ያህሉ መጽደቃቸው ተገልጿል።
በዚህም በአካባቢው መራቆት የተነሳ በቦታው ጠፍቶ የነበረ ምንጭ ዳግም መመንጨቱና የአካባቢው ነዋሪዎችም የደንን ጥቅም ተገንዝበው ጥበቃና እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ወይዘሮ አዳነች በመርሀግብሩ ላይ ” ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ነገ ለብዙ ትውልድ የሚሆን ጥላ፣ ዉበት፣ ልምላሜና የውሃ ምንጭ እንደሚሆኑ ደበል ላይ በተግባር አይተናል” ብለዋል ።
አያዘውም” ስኬታችንን ለማረጋገጥ ችግኞቻችን የሚጸድቁት በያዝናችው እና በተንከባከብናችው ልክ እንደሆነ ማመን እና መተግበር ተገቢ ነው ማለታቸውን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።