አረንጓዴ ዐሻራችሁን በማሳረፍ ላይ ለምትገኙ ሁሉ አድናቆቴ ይድረስ-ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢ. ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አረንጓዴ አሻራችሁን በማሳረፍ ላይ ለምትገኙ ሁሉ አድናቆቴ ይድረስ ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ነው አድናቆታቸውን የገለጹት።
ዶክተር አቢይ አያይዘውም በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ ብለዋል።
አገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በሀዋሳ ከክልል እና ፌደራል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከአካባቢው ሀገር ሽማግሌዎችጋር በመሆን በጋራ በታቦር ተራራ ላይ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።