በባህር ዳር የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ሃይል ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አገልግሎቱ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ በከፍተኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ጉዳት በተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡
ትናንት ምሽት 1 ጀምሮ ከባህር ዳር ቁ.2 የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ በተዘረጋ 15 ኪሎ ቮልት ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ኬብል ላይ በደረሰ ጉዳት በአየርሀይል፣ በመኮድ፣ በአየር መንገድ፣ በውሃ ጉድጓዶች፣ በቀበሌ 14 የኤሌክትሪክ ሃይል ተቋርጧል።
እንዲሁም በቀበሌ 16 ባሉ ፋብሪካዎች፣ በቀበሌ 13፣ በአሚኮ፣ በወገልሳ፣ በዘጌ፣ በላታ፣ በጭንባ፣ በከይባብ፣ በመራዊና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ አቅርቦት መቋረጡን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የተቋረጠውን አቅርቦት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለጸው አገልግሎቱ÷ በአካባቢዎቹ የሚገኙ ደንበኞች ይህንን ተገንዝበው በትግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡