የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ለጎፋ ዞን 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ÷ ኢትዮጵያውያን ክልሉ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ ትብብራቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ድጋፉን በማስረከብ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን መግለጻቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡