የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ጉባዔውን አካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ አካሂዷል።
6ኛው ሀገራዊ የድጋሚ እና የማሟያ ምርጫ በክልሉ መካሄዱን ተከትሎ ምክር ቤቱ ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ጉባዔ ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም የቀድሞ የምክር ቤት አባላቱን መሸቱን ይታወቃል።
ይህን ተከትሎም አዳዲስ የምክር ቤቱ አባላት ቃለ-መሐላ ከፈጸሙ በኋላ የምስረታ ጉባዔው መካሄዱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
ጉባዔው በቆይታው የተለያዩ ውሳኔዎችንም አሳልፏል፡፡
በጉባዔውም አስካለ አልቦሮ የክልሉ ዋና አፈ-ጉባኤ እንዲሁም መለሰ ኩዊ ምክትል አፈ-ጉባዔ ሆነው ተሹመዋል፡፡