የበጎ ፈቃድ ተግባር የሕይወታችን መርኅ መሆን አለበት- አቶ ኦርዲን
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጎ ፈቃድ ተግባር የአንድ ሰሞን ሥራ ሳይሆን በየዕለቱ የሚከናወን የሕይወታችን መርኅ ሊሆን ይገባል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ አስገነዘቡ፡፡
በሐረር ከተማ ለ34 አባወራዎች (129 ቤተሰቦች) የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች እና 10 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ዛሬ ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል፡፡
አቶ ኦርዲን በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ አቅመ ደካሞችን ባሉበት ቦታ ለማደራጀት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን በመጠቆም የተቸገሩትን የመርዳቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡