Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ በመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችን አጽናኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተሰቦች አጽናኑ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ መአራሮች በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በይርጋዓለም ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ የሚገኙ ወገኖችን አጽናንተዋል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን÷ ተጨማሪ መሰል አደጋ እንዳይከሰት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በወረዳው ከትናንት በስቲያ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰዎች ሕይወት መጥፋትን ጨምሮ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.