Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው 18 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ድጋፍ አደረጉ

 

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽንና የፌደራል ፖሊስ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 18 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በጉዳቱ የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

ድጋፉም 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በዓይነት እንዲሁም 5 ነጥብ 4 ሚሊየን በጥሬ ገንዘብ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችና ምግብ ነክ ድጋፎችን አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

በቀጣይም የፖሊስ ህዝባዊ አገልግሎት እንዳለ ሆኖ የተጎዱ ወገኖችን በገንዘብም ሆነ በአይነት የመደገፉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.