Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች አጀንዳቸውን አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ምክክሩ የጋምቤላ ክልል የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች አጀንዳቸውን ለተወካዮቻቸው አስረክበዋል፡፡

በክልሉ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሕብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች ውይይት ተጠናቅቋል፡፡

በውይይቱም ከ14 ወረዳዎች የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል በአጠቃላይ 495 ተሳታፊዎች በአጀንዳነት በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀጣይ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚካሄዱ መድረኮች ላይ ጉዳዮቻቸውን የሚያቀርቡላቸው 60 ተወካዮች በመምረጥ አጀንዳቸውን ማስረከባቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.