በባሕር ዳር ከተማ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ጉዳት በተወሰኑ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ዳግም ወደ አገልግሎት መመለሱ ተገለጸ፡፡
ከትናንት በስቲያ ምሽት 1፡00 ጀምሮ ከባሕር ዳር ቁ.2 የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ በተዘረጋ 15 ኪ.ቮ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ኬብል ላይ በደረሰ ጉዳት በአየር ኃይል፣ መኮድ፣ አየር መንገድ፣ ውሃ ጉድጓዶች፣ ቀበሌ 14 እና 16 ባሉ ፋብሪካዎች፣ ቀበሌ 13፣ 14 እና 16 እንዲሁም በአሚኮ፣ ወገልሳ፣ ዘጌ፣ ላታ፣ ጭንባ፣ ከይባብ፣ መራዊና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ አቅርቦት መቋረጡ ይታወሳል፡፡
የተቋረጠውን አቅርቦት ለመመለስ በተደረገው ርብርብ አገልግሎቱ ዳግም መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡