Fana: At a Speed of Life!

ፓኪስታን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በይበልጥ ማጠናከር እንደምትፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን መንግሥት ለአፍሪካ መግቢያ ከሆነችው ኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት በይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን የሀገሪቱ የመከላከያና አቪዬሽን ሚኒስትር አረጋገጡ፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ከሀገሪቱ መከላከያ እና አቪዬሽን ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ ጋር በሁለትዮሽ፣  ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ላይ መክረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚን በማረጋጋት፣  የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ ምርታማነትን በማሳደግና የስራ ዕድል በመፍጠር እየሰራቸው ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ በበኩላቸው የሀገራቱን ፖሊሲዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የፓኪስታን መንግሥት ለአፍሪካ መግቢያ ለሆነችው ኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል ማለታቸውን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሀገሪቱ ሰላምና ብልፅግናን ለማስረፅ እንደሚረዱም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.