አየር መንገዱ በህንድ 5ኛ የበረራ መዳረሻ ጨመረ On Aug 2, 2024 112 አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በህንድ 5ኛ የበረራ መዳረሻ መጨመሩን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የህንድ የሲቪል አቪዬሽን ሚኒስቴር በፈረንጆቹ ሐምሌ 30 ቀን 2024 ወደ ህንድ ሃይደራባድ ሶስት በረራዎችን ለመጨመር የጋራ መግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተገልጿል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱም አየር መንገዱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በየአቅጣጫው በየሳምንቱ ከ 35 ወደ 38 ለማሳደግ አቅም እንደሚፈጥርለት ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ 112 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint