75 ሺህ ወገኖችን ለመድረስ ያለመ ነጻ የጤና ምርመራ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል 75 ሺህ ወገኖችን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነጻ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት መስጠት ተጀመረ።
አገልግሎቱ በተለይ ከፍለው መታከም የማይችሉ ወገኖችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በመንግሥት ጤና ተቋማት፣ በተመረጡ የግል ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች እየተሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በዚህም የስኳር ህመም፣ የደም ግፊት፣ የዓይን ሕመም ሕክምና እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የነጻ ሕክምና እና ምርመራ እንደሚሰጥ ነው ያስታወቁት፡፡