Fana: At a Speed of Life!

የፀሀይ ግርዶሽ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተከስቷል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀሀይ ግርዶሽ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተከስቷል።

ይህ ቀለበታዊ የፀሀይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ከምእራብ ኢትዮጵያ ወለጋ ተነስቶ በሰሜን በኩል ታይቷል።

በባህርዳር እንጂባራ አካባቢ እስከ 98 በመቶ ጨለማ እንደነበር ነው የተጠቆመው።
በላሊበላ እና በአፋራ አካባቢም በተለያዩ ሰዓታት ላይ ሙሉ ቀለበቱ ታይቷል።

ከማዕከላዊ ኮንጎ የተነሳው ግርዶሹ በኦማን፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ህንድ እና ቻይናን አቋርጦ ማብቂያው ፓስፊክ ውቂያኖስ ነው።

ይህን የፀሃይ ግርዶሽ ለመመልከት ከዓለም ላሊበላ አመቺ ስፍራ የነበረ በመሆኑ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተመራማሪዎች እና ጎብኚዎች ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የተመዘገቡ ቢሆንም፥ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት መምጣት አልቻሉም።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.