የፌደሬሽን ምክር ቤት በቡታጅራ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት ስራዎችን አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬሽን ምክር ቤት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎችን አስጀምሯል፡፡
የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰውና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤትና ተጠሪ ተቋማቱ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
በመርሐ ግብሩም የችግኝ ተከላ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና ለ300 ተማሪዎች የመማርያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የምክር ቤቱ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ይህ አራተኛው ዙር ነው።
በአሸናፊ ሽብሩ