Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሥራ ሃፊዎችና አባላት ኮልፌ በሚገኘው የልዩ ፀረ ሽብር መምሪያ ግቢ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል÷ ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት ከህብረተሰቡ ጎን በመሆን በልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ እንዲሁም አቅመ-ደካሞችን በመደገፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የዛሬው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ የምትከተለውን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ላይ አሻራችንን ማሳረፍ ነው ብለዋል።

ፖሊስ ሰላምና ፀጥታን በማስከበር እና ሀገራዊ ተልዕኮውን በመወጣት እያስመዘገባ ካለው አመርቂ ውጤት ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይም በስፋት በመሳተፍ የድርሻውን እያበረከተ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ በማሳደግ ለፍሬ እንዲበቁ ማድረግ ይጠበቅብናልም ማለታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዛሬው ዕለት ከተተከሉ ሀገር በቀል ችግኞች መካከል ለምግብነት የሚውሉ እንደ ማንጎና አቮካዶ የመሳሰሉ የፍራፍሬ ችግኞችም ይገኙበታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.