Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ በ2ኛው ምዕራፍ የትብብር ማዕቀፍ በ7 ዋና ዋና የልማት መስኮች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያና ቻይና በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ ለዓመታት የዘለቀ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል።

ከፋውንዴሽኑ ጋር የተደረገው ስምምነትም የዚሁ ዘመናትን የተሻገረ የእርስ በርስ ጠንካራ ወዳጅነትና ትብብር አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ፕሮጀክቶቹ በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ ጠቅሰው፥ ውጤታማ እንዲሆኑም ሚኒስቴሩ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

የፋውንዴሽኑ ካንትሪ ዳይሬክተር ይን ቼን በበኩላቸው ÷ በተጠቀሱት ዘርፎች አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ቻይና በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ አስተዋጽኦ እያበረከተች እንደምትገኝ መጠቆሙን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.