Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5 ሠዓት ገደማ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

እስከ አሁን የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መረጋገጡን እና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል መገለጹን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከክረምቱ ማየል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደራሽ ውኃ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የሚያስከትሉት አደጋ በመሆኑ ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.