Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖች ጋር ተወያዩ።
 
ከመከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች ጋር በአዲሱ የመከላከያ ግንባታ ስትራቴጂ ዝግጅት እና በተቋማዊ የግንባታ ሂደት ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ወቅታዊ አገራዊ ፈተናዎችን ባገናዘበ መልኩ እንዲሁም ዓለማቀፋዊ የወታደራዊ አቅምን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀው ሰነዱ ለህገመንግስቱ ተገዢ የሆነና ለህዝብና አገር ዘብ የቆመ ሠራዊት ለመገንባት ያግዛል ብለዋል፡፡
 
የካቲት ወር 2012 ዓ.ም ላይ የታተመው ረቂቅ የሥትራቴጂክ ሰነዱ በሂደት እየዳበረ ሁሉም ዜጋ በቀላሉ እንዲረዳው እንዲያውቀውና በጊዜ ሂደት ከወቅቱ ጋር እየተናበበ እንዲሻሻል ተደርጎ የሚቀረጽ ሲሆን በአዲስ መልክ ለማዘጋጀት ያስፈለገው ሠራዊቱን ለማዘመን በማለም መሆኑንም ገልፀዋል።
 
ይህን ሰነድ በድጋሚ በትኩረት ለመመልከት ያስፈለገበት አምስት መሠረታዊ እውነታዎች አሉ ያሉት ጠቅላይሚኒስትሩ እነዚህን አመክንዮዎች በመለየት ሰነዱ እንዲሻሻል ተደርጓል ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል፡
 
ጠቅላይ ሚስትሩ በማብራሪያቸው እንዳነሱት የሠራዊት ግንባታ ስትራቴጂው የአገሪቱን ሉዓላዊነት ባስከበረ መልኩ ህዝቦቿ የሚተማመኑበት ዳር ድንበሯን የሚያስከብርና ዓለማቀፍ ተቀባይነቷ እንዲጨምር በሚያስችል መልኩ እንደተሰናዳም አስረድተዋል፡፡
 
የመከላከያ ሰራዊቱ ለፓርቲ ለብሔርና ለቡድን የወገነ ሳይሆን አገራዊ ሉዓላዊነትን መሠረት አድርጎ በህገመንግስቱ የሚመራ ሆኖ አገራዊ ቀጣይነትን ማረጋገጥ አለበት ብለዋል፡፡

 

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.