አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ጌትነት ዋለና ሳሙኤል ፍሬው ለፍጻሜ ደረሱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ለሜቻ ግርማ፣ ጌትነት ዋለና ሳሙኤል ፍሬው ለፍጻሜ አልፈዋል።
አትሌት ጌትነት በምድብ አንድ 3ኛ ፤ ሳሙኤል በምድብ ሁለት 2ኛ እንዲሁም ለሜቻ በምድብ ሶስት 1ኛ ደረጃን በመያዝ ነው ለፍጻሜ የደረሱት፡፡
የፍጻሜ ውድድሩም ረቡዕ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ43 ደቂቃ ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡