የብሔራዊ ስታዲየም ምዕራፍ 2 ሎት 1 የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት የብሔራዊ ስታዲየም ምዕራፍ ሁለት ሎት አንድ የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ÷ የሲቪልና የኤሌክትሪክ ሥራዎች፣ የመኪና ማቆሚያ፣ የመንገድ፣ የወንበር ገጠማ እንዲሁም የአጠቃላይ ገጽታ (የላንድስኬፕ) ሥራዎችን ያካተተ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የውጭ ምንዛሪ የማይጠይቁ ሌሎች ሥራዎች በሀገር ውስጥ በጀት እንደሚከናወኑ እና በቅርቡም ጨረታ ወጥቶ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።