የአብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ የጦር ነጋሪት መጎሰም ተቀባይነት የለውም – በተመድ እውቅና ያለው የሊቢያ መንግስት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታታት ድርጅት እውቅና ያለው የሊቢያ መንግስት የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ያስተላለፉት የጦርነት ጉሰማ ተቀባይነት የለውም አለ።
አል ሲ ሲ በተባበሩት መንግስታታት ድርጅት እውቅና ያለው የሊቢያ መንግስት የግብፅ እና የጄኔራል ካሊፍ ሃፍታር ጦር ቀይ መስመርን እንዳያልፍ ሲሉ በትናትናው ዕለት ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈው ነበር።
ቅዳሜ ዕለት በሊቢያ አቅራቢያ በሚገኘው የግብፅ አየር ሀይል ጣቢያ በተገኘቡት ወቅት እንደተናገሩት አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ ጦር ወደ ሊቢያ ሀገራቸው እንደምትልክ ገልፀዋል።
ይህንን ተከትሎ በተባበሩት መንግስታታት ድርጅት እውቅና ያለው የሊቢያ መንግስት የምክር ቤት አባል የሆኑት አብዱርሃማን ሻተር ሊቢያ ያልተቀበለችው የግብፅ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በሊቢያ ዲሞክራሲን አደጋ ላይ ጥሏል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
አብዱርሃማን ሻተር ከእኛ ላይ እጃችሁን አንሱ በየመን የፈፀማችሁትን አሰቃቂ ድርጊት እንዳትደግሙት ሲሉ ነው በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።
ግብፅ በሊቢያ የውስጥ ጉዳይ እጇን ካስገባች አራት አመት እንደሆናትም ገልፀዋል።