Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ ለኢትየጵያ የ7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያ መንግስት በኢትየጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ድጋፉ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ)፣ በዓለም ምግብ ፕሮግራም (ደብሊዩኤፍፒ)፣ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማሕበር (አይሲአርሲ) እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በኩል ተደራሽ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

በዚህም ድጋፉ በግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለችግር ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚውል ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ድጋፉ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረት እንደሚውል ነው የተመላከተው፡፡

ደቡብ ኮሪያ ያደረገችው ድጋፍ በዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች አማካይነት የሚሰራጭ መሆኑን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በሰብዓዊ እርዳታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበትና በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጣለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.