በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከተሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ፡፡
ድጋፉን ያደረጉት ከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ እንዲሁም አዋሽ ባንክ ሲሆኑ÷ በዚሁ መሠረት ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ 3 ሚሊየን እና ባንኩ ደግሞ 7 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና በአዋሽ ባንክ የወላይታ ሶዶ ሪጂን ዳይሬክተር ዘላለም በቀለ ድጋፉን ለዞኑ አስረክበዋል፡፡
የጎፋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ (ኢ/ር) እና የጎፋ ዞን ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ሐብታሙ ፈተና ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት ምስጋና አቅርበዋል፡፡