Fana: At a Speed of Life!

ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚከናወነው ሥራ የሕብረተሰቡ ሚና ወሳኝ ነው – አቶ አሻድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠላም እና ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ለሚገኙ ተግባራት ውጤታማነት የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

በክልሉ የተካሄደውን የመንግሥት ምስረታ እንዲሁም መንግሥት እያከናወነ ለሚገኘው የሠላምና የልማት ሥራ ዕውቅና ለመስጠት ያለመ መርሐ-ግብር በቡልድግሉ ወረዳ ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅት አቶ አሻድሊ ባደረጉት ንግግር÷ የነበሩ የጸጥታ ችግሮችን በመፍታት ሠላምን ለማረጋገጥ ለተሠሩ ሥራዎች ውጤታማነትና ለተመዘገበው አንጻራዊ ሠላም መሣካት የክልሉ ሕዝብ የላቀ ሚና አበርክቷል ብለዋል፡፡

በጸጥታ ችግር ውስጥ ያሳለፍናቸው ዓመታት ለልማት ሊውል የሚችል በርካታ ሀብት አሳጥቶናል ያሉት አቶ አሻድሊ÷ አሁን የተገኘውን ሠላም ዘላቂ በማድረግ ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የወረዳው ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ በክልሉ ሠላምን ለማረጋገጥ እና የሕብረተሰቡን ጥያቄዎች ለመመለስ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ሠላም እና ልማትን ለማረጋገጥ ለሚያከናውናቸው ሥራዎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.